Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ምዕራባውያን ቃል የገቡትን “የሎጂስቲክስ ማዕቀብ” አላነሱም ስትል ወቀሰች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እህል እና ማዳበሪያ ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ ምዕራባውያኑ የገቡትን ቃል አላከበሩም ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ወቀሱ።

ምዕራባውያን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ላይ የተጋረጠውን የምግብ እህል አቅርቦት ቀውስ ለማቃለል በተመድ እና ቱርክ አደራዳሪነት የዩክሬን የእህል ምርት በጥቁር ባሕር በኩል ለዓለም አቀፉ ገበያ እንዲቀርብ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሩሲያ እህል እና ማዳበሪያ ለዓለም አቀፉ ገበያ ያለ ገደብ እንድታደርስ ስምምነት ቢደርሱም ይህን አላከበሩም ሲሉ ነው ሚኒስትሩ የወቀሱት።

በቱርክ ኢስታንቡል የተደረሰው ሥምምነት የጥቁር ባሕር ወደብ እንዲከፈት እና ከዩክሬን በወጪ ንግድ የሚላከው የምግብ እህል አቅርቦት እንዲቀጥል ነበር፡፡

ምዕራባውያኑ ግን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኩል የገቡትን ቃል አላካበሩም ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቅርበዋል።

የሩሲያ እህል እና ማዳበሪያ ወደ ዓለም ገበያ እንዳይገባ የሚከለክለውን የ”ሎጂስቲክስ ማዕቀብ” አላነሱምም ነው ያሉት ሰርጌይ ላቭሮቭ፡፡

ሚኒስትሩ ከታይላንድ አቻቸው ዶን ፕራሙድዊናይ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተመድ ኢስታንቡል ላይ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ግዴታውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.