Fana: At a Speed of Life!

የ9/11 የአሜሪካው የሽብር ጥቃት ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ መስከረም 11 ቀን 2001 የተፈጸመው የ9/11 የአሸባሪዎች ጥቃት 21ኛ ዓመት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በታደሙበት ሥነ-ሥርዓት በፔንታጎን ታስቦ ዋለ፡፡

እንደሚታወሰው በፈረንጆቹ መስከረም 11፣ 2001 ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ታጣቂዎች አራት አውሮፕላኖችን ጠልፈው ኒውዮርክ በሚገኙት የዓለም ንግድ ማዕከል መንታ ህንፃዎች እና በአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የአጥፍቶ መጥፋት የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ሁለቱን አውሮፕላኖች ኒውዮርክ ከሚገኙት የዓለም ንግድ ማዕከል መንታ ህንፃዎች ጋር በማጋጨት የአጥፍቶ መጥፋት ተግባር ፈጽመዋል፡፡

ሦስተኛው አውሮፕላን ደግሞ ወደ አርሊንግተን ቨርጂኒያ በማምራት ከፔንታጎን ጋር ተላትሟል፡፡

አራተኛው አውሮፕላንም ሻንክስቪል ፔንስልቬንያ ባለ ሜዳ ላይ ወድቆ መከስከሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሽብር ጥቃቱ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት ማለፉንም የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡

በሽብር ጥቃቱ ላይ የተሳተፉት 19 ታጣቂዎች መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.