ከ21 የኮሜሳ አባል ሀገራት ኤምባሲ ተወካዮች ጋር በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ21 የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) አባል ሀገራት ኤምባሲ ተወካዮች ጋር በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማበረታት ያለመ ውይይት ተካሄደ፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሚልኬሳ ጃገማ እንደተናገሩት ፥ የአፍሪካ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንስቲትዩት የአባል ሀገራቱን ቆዳና ሌጦ እሴት በመጨመር ድህነትን በመቀነስ፣ የስርዓተ ፆታ እኩልነት፣ የስራ እድል ፈጠራና አህጉራዊ ውህደት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
ኢንስቲትዩት በኮሜሳ ቀጣና እና በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ አባል ሀገራቱን የቆዳ እሴት ሰንሰለት ልማትን ለማጎልበት በ17 የኮሜሳ አባል ሀገራት የተቋቋመ መንግስታዊና እውቀትን መሰረት ያደረገ ድርጅት ነው፡፡
የውይይቱ ዓላማም በአፍሪካ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንስቲትዩት የሀገራት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።