በአየር ንብረት ላይ የሚመክረው የአፍሪካ ሚኒስትሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ንብረት ላይ የሚመክረው 18ኛው የአፍሪካ ሚኒስትሮች ጉባኤ በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ ነው፡፡
ሚኒስትሮቹ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የጤና፣ የምግብ፣ የኃይል እና የገንዘብ ቀውስ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ከዚህ ባለፈም በአየር ንብረት ለውጥ እና በህዝቦች ደህንነት ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ የሴኔጋል የአካባቢ እና ዘላቂ ልማት ሚኒስትር አብዱ ከሪም ሳል በጉባኤው መክፈቻ ተናግረዋል፡፡
አህጉሪቱን እና ህዝቦቿን አደጋ ላይ የሚጥሉ በርካታ የአየር ንብረት ቀውሶችን ለመቀነስ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባም በጉባኤው ተነስቷል ።
የዜጎችን ስራ አጥነት በሚቀንሱ እና ኑሮን በሚያሻሽሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ በጋራ እንደ አንድ አህጉር መስራት ይገባል መባሉን ሺንዋ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!