Fana: At a Speed of Life!

የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ማዕቀቦች መነሳት አለባቸው- ኢራን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሜሪካ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ማንሳት እንዳለባት ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መርሐ ግብሯ በዘላቂነት ለማስወገድ ከአሜሪካ በኩል አስተማማኝ ዋስትና ልታገኝ ይገባል ብለዋል።

ከአሜሪካ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ጊዜው ገና እንዳልሆነ ጠቅሰው ከቴህራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ በፈለገችው ዋሺንግተን ቅንነት ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸውም ገልጸዋል።

ማዕቀቦችን ማንሳት የመፍትሄ አካል መሆን አለበት ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ጉዳዩን በጥንቃቄ ለመቋጨትም በኢራን ላይ የሚነሱ ፖለቲካዊ እና መሠረተ ቢስ ውንጀላዎች ሊቆሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዋስትናዎችን በተመለከተ የተጣሉ ማዕቀቦችን በዘላቂነት ማንሳት እንጂ ጊዜያዊ እርምጃ እንደማይፈልጉ ጠቅሰዋል፡፡

ለጉዳዩ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሄ ከተገኘ በእርግጠኝነት ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.