Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት እንዲጠናከር በልዩ ትኩረት እንሠራለን – የደ/አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኬሲ ማሼጎ ድላሚኒ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ሙክታር በኢትዮጵያ ስለለው ወቅታዊ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ግጭቱ እንዲከሰት፣ እንዲባባስና መፍትሔ እንዳይገኝ ሀገር የማፍረስ እኩይ ተግባሩን እንደቀጠለበት ጠቁመው÷ በአንጻሩ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰላም ፈላጊ መስሎ ለመታየት የማጭበርበር ተግባሩን እንደቀጠለበት አስረድተዋል፡፡

ኬሲ ማሼጎ ድላሚኒ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ለአፍሪካ ቀንድና ለአህጉሩ ሰላም ከፍተኛ ፈይዳ አለው ማለታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ለሦስተኛ ጊዜ የከፈተው ጦርነት ደቡብ አፍሪካን እንደሚያሳስባት ገልጸው÷ ሀገራቸው ግጭቱ ቆሞ ሰላም እንዲሰፍንና ለጉዳዩ በድርድር ላይ የተመሰረተ መፍትሄ እንዲሰጠው ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር በትኩረት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.