Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 200 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ከ200 በላይ የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን በመጠበቅ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግድ ተቋማት ላይ የንግድ ፍቃድ የመቀማትና ለህግ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮው ሃላፊ አቶ ዴንጌ ቦሩ ተናግረዋል።

ለዚህም ከክልል እስከ ወረዳ ችግሩን የሚከታተል ግብረ ሃይል መቋቋሙንም ነው ሃላፊው የገለጹት።

የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠርና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር የህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች ምርቶችን በስፋት እንዲያቀርቡ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ችግርን ከማባባስ ይልቅ ከሀገር እና ከዜጎች ጎን በመቆም የመፍትሄ አካል እንዲሆኑም አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግድ ተቋማትን ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በዙፋን ካሳሁን እና በዘመን በየነ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.