Fana: At a Speed of Life!

የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተገናኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር የማገናኘት ሥራ በስኬት መከናወኑ ተገለጸ፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጁ ሙሉቀን ተሰማ እንደተናገሩት ÷ 40 ሜጋ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 16 የንፋስ ተርባይኖች የፍተሻና ሙከራ ሥራ ተጠናቆ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የማገናኘት ሥራ ተሰርቷል፡፡

በቀጣይም 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ የንፋስ ተርባይኖች የፍተሸና ሙከራ ሥራን በማጠናቀቅ ጣቢያው 80 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲያመነጭ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል፡፡

የፕሮጀክቱ አብዛኛው ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁመው ፥ አጠቃላይ አፈፃፀሙም 80 በመቶ መድረሱን ነው ያነሱት፡፡

በጣቢያው ሊገነቡ ከታሰቡት 48 የንፋስ ተርባይኖች መካከል 32 ያህሉ መተከላቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

ቀሪዎቹን 16 ተርባይኖች ለመትከል መሰረት የማውጣት ሥራ ቢጠናቀቅም በገንዘብ ችግር ምክንያት ተርባይኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አለመቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡

ፕሮጀክቱ ያጋጠመውን የገንዘብ ችግር ለመፍታት የተቋሙ ሥራ አመራርና ቦርድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ በቅርቡ መፍትሔ ያገኛል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.