Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረምን እያስተናገደች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

“ቀጠናዊ የክህሎት እና የወጣቶች ሥራ ስምሪት” ቴክኒካል ቡድን ለማቋቋም በተደረገው ስምምነት መሠረት የአባል ሀገራቱ የቴክኒክ ቡድን ማቋቋሚያ ስብሰባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፎረሙ 11 ሀገራት የሚገኙበት እና የሠራተኛ ፍልሰትን ጉዳይ የሚመሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያቀፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረምን በሊቀመንበርነት እየመራች እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.