የምክር ቤቶቹ አባላት ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድን ጨምሮ የሁለቱ ምክር ቤት አባላትና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል።
“ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ያካሄዱት የሁለቱ ምክር ቤቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ ይገባል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በደም ልገሳ፣ በገንዘብ እና በአይነት የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!