Fana: At a Speed of Life!

ወንጀል ነክ ጉዳዮች ውስጥ የገቡ ሕፃናት ማቆያ እና ተሃድሶ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ሆኖ ወንጀል ውስጥ ተሳትፈው የተገኙ ሕፃናት እና ታዳጊዎች ማረሚያ ማዕከል ከ450 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ ዛሬ ተመረቀ፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚገኘው ይህ ተቋም ከ70 ዓመት በፊት በ1936 ዓ.ም እንደተመሰረተ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ አሁን ላይ ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ እና ረጅም ዘመን ስላስቆጠረ ህንጻውን በአዲስ መልክ መገንባት አስፈልጓልም ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም 150 ታራሚዎችን ብቻ ሲያስተናግድ የነበረው ተቋሙ አሁን ከ700 በላይ ታራሚዎችን በማዕከሉ ማቆየት ያስችላል ተብሏል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.