ህንድ በተለዋጭ አባልነቷ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያሳየችው አቋም የሚደነቅ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያሳየችውን ገለልተኛ እና መርህን የተከተለ አቋም ኢትዮጵያ አደነቀች።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማኒያም ጃይሸንከር ጋር ከ77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እና የኢኮኖሚ ማሻያዎች እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ ባለፈም አሸባሪው ህወሓት ስለከፈተው ጥቃት እና መንግስት በሰሜኑ ያለውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየወሰደ ያለውን እርምጀ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
አቶ ደመቀ አያይዘውም ህንድ በአስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያ ላሳየችው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ህንድ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያሳየችው ትክክለኛ፣ ገለልተኛ እና መርህን የተከተለ አቋም የሚደነቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማኒያም ጃይሸንከር ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አንስተው ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እድሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸው ህንድ የደቡ – ደቡብን በባለብዙ ወገን መድረክ እንደወከለች እንዲሁም ከምግብና ነዳጅ አቅርቦት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር ለሳየቸው ተነሳሽነት እውቅና ሰጥተዋል።
አቶ ደመቀ መኮንን በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የትምህርት ለውጥ ጉባዔ ላይ የተገኙ ሲሆን ፥ በሁነቱ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ንግግር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኒውዮርክ በሚኖራቸው ቆይታ ከጉባዔው ጎን ለጎን ሌሎቸ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!