Fana: At a Speed of Life!

ቻይና 3 የአሜሪካ ጋዜጠኞችን አገደች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ሶስት የአሜሪካ ጋዜጠኞች ማገዷን አስታወቀች።

እርምጃው አሜሪካ ውስጥ በሚሰሩ የቻይና ጋዜጠኞች ላይ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተጣለው እገዳ አፀፋዊ ምላሽ ነው ተብሏል።

የታገዱት ጋዜጠኞች ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዋሽንግተን ፖስት እና ዎል ስትሪት ጆርናል ላይ የሚሰሩ መሆናቸውም ተመላክቷል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጠኞቹ የሚዲያ የይለፍ ፈቃዳቸውን በ10 ቀናት ውስጥ እንዲመልሱም አዟል።

ከዚህ በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋዜጦቹ ቻይና ውስጥ ስለሚሰሩት ስራ ዝርዝር መረጃ እፈልጋለሁ ብሏል።

መስሪያ ቤቱ እንደ ሆንግ ኮንግ እና ማካው ባሉ ከፊል ራስ ገዝ አካባቢዎች ጋዜጠኞች እንዳይሰሩም አግዷል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ትራምፕ አሜሪካ በሚገኙ የቻይና ጋዜጠኞች ላይ ገደብ መጣላቸው ይታወሳል።

የአሁኑ እርምጃ ሃገራቱ የገቡትን ፍጥጫ እንዳያባብሰው ተሰግቷል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.