በ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከ60 በላይ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የውሃ አና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የውሃ መሰረተ ልማቶች ትኩረት ይሰጣል፡፡
በዘንድሮው ዓመትም የዞን እና የወረዳ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ፕሮጀክቶች ይገነባሉ ነው ያሉት፡፡
ከዚህ በፊት ግንባታቸው የተጀመረ የውሃ ፕሮጀክቶች አብዛኛዎቹ እንደሚጠናቀቁም ገልጸዋል፡፡
የውሃ ጥራት ችግሮችን ለመፍታት ዓለም ዓቀፍ ሕግ እና አስፈላጊው መሰረተ ልማት እየተሟላ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በአልማዝ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!