Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ጎጃም ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመመከት በግንባር ለተሰለፈው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ÷ አሸባሪው ህወሐት ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት የከፈተው ከልማት ስራዎቻችን ለመነጠል አልሞ ቢሆንም ልማቱን በማስቀጠል ፤ ጦርነቱን መመከት ግዴታችን ነው ብለዋል።
 
የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበርና ልማት የማይነጣጠሉ ገጽታዎች መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ መልካሙ÷ ዞኑ ለሰራዊቱ ድጋፍ እንዲውል ህዝቡንና ባለሃብቱን በማስተባበር ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መገኘቱን ገልጸዋል።
 
ከዚህ ገንዘብ ወስጥ 16 ሚሊየን ብር የሚሆን የደረቅ ሬሽንና የእርድ እንስሳት ግንባር ለመላክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
 
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመደገፍ ህዝቡ የጀመረውን የደጀንነት ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.