Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ተዓማኒ ያልሆነ፣ ሙያዊ አካሄድን ያልተከተና ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ ነው – አምባሳደር ዘነበ ከበደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ሪፖርት ተዓማኒ ያልሆነ፣ ሙያዊ አካሄድ ያልተከተና ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ ነው ሲሉ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ገለጹ።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ላይ አሳታፊ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እንዲያጣራ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ለሪፖርቱ በሰጡት ምለሽ÷ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ተዓማኒ ያልሆነ፣ ሙያዊ አካሄድን ያልተከተና ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ ሰብዓዊ መብቶችን እንደምታከብር ያረጋገጡት አምባሳደሩ÷ የኮሚሽኑ ሪፖርት በሰብዓዊ መብት ሽፋን ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለመውጥ ለመቀልበስ እና በሀገሪቱ በህዝብ የተመረጠውን ህጋዊ መንግስት በሃይል ለመገልበጥ ጦርነት መክፈቱን አንስተዋል፡፡

የቀረበው ሪፖርት ከዚህ በፊት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ላደረጉት የጋራ ምርመራ እውቅና ያልሰጠ እና ዝቅ ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.