Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በዞኑ አልከሶ 01 ቀበሌ መኒታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በ3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል፡፡

የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል እንደገለጹት÷ አደጋው የተከሰተው ሀይሉክስ ተሽከርካሪ ከባለሶስት እግር ተሽከርካሪ  በመጋጨቱ ነው ብለዋል።

ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ህፃን ልጅ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን÷ በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ መሆኑን ምክትል ሳጅን ቢላል አወል መናገራቸውን ከወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.