በ13ኛው ዙር እጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውል ስምምነት የወሰን ውዝግብ ያለባቸውን እንደማያካትት ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ13ኛው ዙር እጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተከናወነ ያለው የውል ስምምነት የወሰን ውዝግብ ያለባቸውን ቤቶች እንደማያካትት ተገለፀ።
ሰሞኑን በተለያየ የግል ምክንያት እጣ ወጥቶላቸው ውል ያልተፈራረሙ እድለኞችን ውል የማፈራረም ስራ እተከናወነ ይገኛል።
ቤቶቹን የማስተላለፍ አካል የሆነው የውል ሰምምነት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የወሰን ጥያቄ የተነሳባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደማያካትት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የወሰን ጥያቄ የተነሳባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ በፌደራል መንግስት በተቋቋመው ኮሚቴ፣ በኦሮሚያ ክልል እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል እየታየ እንደሚገኝም ገልጿል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision