Fana: At a Speed of Life!

ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ከአምባሳደር ካትሪን ስሚዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካትሪን ስሚዝን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ የዴንማርክ መንግሥት በክልሉ ደን ሀብት አጠባበቅ እና የማኅበረሰብ የኑሮ ማሻሻያ ላይ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

 

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የደን ሀብቶችን የማስፋትና ስነ ምህዳርን የመጠበቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ለአምባሳደሯ አስረድተዋል፡፡

 

አምባሳደር ካትሪን ስሚዝ ክልሉን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው÷ በዘርፉ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በዴንማርክ መንግሥት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ደንን መሰረት ያደረገ የኑሮ ማሻሻያ ድጋፍ ላይ እየተሠሩ ያሉ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን ጎብኝተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.