Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ እና ጂቡቲ ከተሞች ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ እና የጂቡቲ ከተሞች ህዝብ ለህዝብ በባህል፣ ቱሪዝም፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰት፣ መሰረተ ልማት አቅም ግንባታ ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ።

በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እና በጅቡቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰዒድ መሃመድ መካከል የተፈረመው ሰነዱ መፈረሙን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህም በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ ጥልቅ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ትስስር እውቅና ከመስጠቱም ባሻገር በአገራችን እና ጅቡቲ መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚገኘውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጠናክር እንደሆነ ታምኖበታል።

የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ እና ልዑካን ቡድኑ በጂቡቲ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጋር በመሆን 62 ሺህ ችግኞች ለጂቡቲ ከተማ ከንቲባና ለጂቡቲ ግብርና፣ እንስሳት እና አሳ ሀብት ሚኒስቴር ተወካዮች አስረክበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.