Fana: At a Speed of Life!

የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ሊከበር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ ፋውንዴሽን የጀነራሉን 100ኛ ዓመት የልደት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሊያከብር መሆኑን ገለጸ።

ፋውንዴሽኑ የበዓል አከባበሩን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፥ የበዓሉ መከበር ዋነኛ ምክንያት አሁን ያለው ትውልድ የጄኔራሉን ታሪክ በማወቅ ተግባራቸውን እንዲወርስ እና ለአገሩ አስተዋጽኦ እንዲያደረግ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ፋውንዴሽኑን ለመደገፍ ታስቦ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በዚህ ወቅት ብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ ትምህርት ለሰፊው ህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ታላቅ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የበዓሉ አከባበርም ከጥቅምት 13 ቀን ጀምሮ ባሉ አራት ተከታታይ ሳምንታት የሚከበር ይሆናልም ነው የተባለው።

የበዓሉ አከባበርም በተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚካሄድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፥ የጀነራሉን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ምርቃት፣ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ በአካል ጉዳተኞች መካከል የሚካሄድ የቴሌቪዥን ጥያቄና መልስ እንዲሁም በፎቶ አውደ ርዕይ የሚከበር መሆኑም ተገልጿል።

ብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ ” የተማረ ሰው መብቱን ይጠይቃል ” በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ።

ብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ ለህዝብ ትግል ብለው የተሰዉ ጀግና መሆናቸውም በዚሁ መግለጫ ወቅት ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.