የኢትዮጵያ መንግሥት በባርቲን ግዛት በተከሰተ ፍንዳታ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ትናንት በቱርክ ባርቲን ግዛት በድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የተሰማው ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በአደጋው ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ለቱርክ ሕዝብና መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ÷ በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በተከሰተው አደጋ እስካሁን የ41 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!