በሶማሌ ክልል በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ለተሠማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳሽን ባንክ በሶማሌ ክልል በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች ለተሠማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በብድር የሚሰጥ 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ባንኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ የክልሉ የክህሎትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ ሁሴን ጌዲ እና ሌሎች የክልሉና የዳሽን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ድጋፉን አስረክቧል።
ከወለድ ነፃ የብድር አገልግሎት ለማቅረብ ባንኩ ከክልሉ መንግሥት ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት የተደረገ ድጋፍ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
በተደረገው የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ እናቶችንና ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።