ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የገነባውን የሰራዊት መኖሪያ ቤት መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የገነባውን የሰራዊት መኖሪያ ቤት መርቀው ከፍተዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት ÷የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የአየር ሃይል አባላትን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በአጭር ጊዜ ሰርቶ ያስረከበው ቤት የሚያስመሰግን ነው።
በዕለቱም በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ብ/ጀኔራል ደረጄ መገርሳ የተመራ ሉዑክ በዋና መምሪያው ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችንና በግንባታ ሒደት ላይ የሚገኘውን የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መጎብኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡