Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ከፋኦ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የምግብ ፎረም ጎን ለጎን ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ቁ ዶንግዩ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ አቶ ዑመር ለዋና ዳይሬክተሩ በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ስለተደረገው ማሻሻያ፣ የዘርፉ ስኬቶች እና መንግሥት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርናን ለመተግበር እያደረገ ስላለው ጥረት ገለጻ አድርገዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ማድነቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.