Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከእንግሊዝ የልማት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከእንግሊዝ የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይታቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መምክራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ በዚሁ ወቅት እንግሊዝ የኢትዮጵያ ጠንካራ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰው የሀገራቱን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው÷ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.