አንዳንድ ምዕራባውያን በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ በመግባታቸው ለሰላማችን እንቅፋት ሆነዋል- የደሴ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ የምዕራባውያን ሀገራት በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ በመግባታቸው ለሰላማችን እንቅፋት ሆነዋል ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በደሴ ከተማ አሸባሪው ህወሓትን እና የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓት እና ምዕራባውያን ሀገራት በሀገራችን ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ ሊገቡ አይገባም ሲሉ አውግዘዋል፡፡
በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባታቸውም ለውስጥ ሰላማችን እንቅፋት ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
ሰልፈኞቹ ÷ አሸባሪው ህወሓት የችግር ምንጭ ነው፣ ጠላታችን ህወሓት እንጅ የትግራይ ሕዝብ አይደለም፣ በውክልና ጦርነት መጠቃታችን ይብቃ፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሱለይማን እሸቱ ባደረጉት ንግግር÷ በህልውናችን ለመጡብን ነበልባል መሆናችንን አይደለም ወዳጆቻችን ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቃሉ ብለዋል፡፡
የሉዓላዊነት ጉዳይ ለድርድር የምናቀርበው አለመሆኑን ተገንዝበው የውጭ ኃይሎች ጣልቃ እንዳይገቡብን እንጠይቃለን ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን የውስጥ ሰላም ማስከበር ለቀጠናው ሰላም የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን በመገንዘብ ሊደግፉ ሲገባ÷ የሽብር ቡድኑን ዕድሜ ለማራዘም የሚያደርጉትን ጥረት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች አውገዘዋል ብለዋል ክትል ከንቲባው፡፡
በአንድነት ናሁሰናይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!