Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ልዑክ በአቦቦ ወረዳ እየለማ የሚገኝ የስንዴ ማሳን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በአቦቦ ወረዳ በአንድ ባለሃብት እየለማ የሚገኝ የስንዴ ማሳን ጎብኝቷል፡፡

አቶ ኡሞድ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ እየተከናወነ ባለው ሥራ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ መመልከታቸውን አንስተዋል፡፡

በወረዳው የተሞከረው የስንዴ ልማት በክልሉ በሰፊው ስንዴን ለማምረት የሚያስችል አቅም መኖሩን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

በስንዴ ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ተሞክሮውን ወደ አርሶ አደሩ እርሻ የማስፋት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

በክልሉ የቆላ ስንዴን በስፋት ለማልማት የሚያስችል ሰፊ ዕድል በመኖሩ የሚመለከታቸው አካላት በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ መቅረቡንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.