Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የበኩላችንን ሚና እንወጣለን – በአስተዳደሩ የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በከተማ አስተዳደሩ የሚኖሩ የሐረሪ ክልል ተወላጆች ገለጹ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ÷በከተማዋ የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የሐረሪ ክልል ተወላጆች በአስተዳደሩ የልማት ፣ የመልካም አስተዳደርና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና ከመወጣት አኳያ ያሉባቸው ውስንነቶች እንደሚቀርፉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የአስተዳደሩን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የድርሻቸውንመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነውያረጋገጡት፡፡

አስተዳደሩም በአስፈላጊው መስኮች ሁሉ ተወላጆቹን ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆነ መገለጹን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.