Fana: At a Speed of Life!

ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
ኮሚሽኑ ከጥቅምት 4 ቀን እስከ 10 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 99 ነጥብ 2 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 31 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡
 
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ውሰጥ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሃኒት፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
 
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን÷ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 11 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
 
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋና ማቅረቡንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.