Fana: At a Speed of Life!

በአላማጣ አሸባሪው ህወሓት ለታጣቂዎቹ አከማችቶት የነበረው ከ3 ሺህ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ለራያ አላማጣ ህዝብ የሚመጣውን የእርዳታ እህል ለህዝቡ ሳያደርስ ለታጣቂዎቹ ቀለብ እንዲውል በየመጋዝኖቹ እና ወፍጮ ቤቶች አከማችቶት ተገኝቷል።

በአላማጣ ከተማ በተለያዩ የእህል መጋዝኖችና ወፍጮ ቤቶች ከ2 ሺህ 500 ኩንታል በላይ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) የተፈጨ የስንዴ ዱቄት፣ ከ400 ኩንታል በላይ በዩኤ ስ አይ ዲ ከረጢት የታሸገ ስንዴ፣ ከ100 ኩንታል በላይ ብስኩቶች እና ኃይል ሰጪ ምግቦች ናቸው ተከማችተው የተገኙት።

የሽብር ቡድኑ ካለፈው 1 ዓመት ከ4 ወር በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሰብዓዊ እርዳታ እንዲውል የሚገባ የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ከህዝቡ እየነጠቀ ለታጣቂዎቹ ሲያከማችና ሲቀልብ እንደነበር ነዋሪዎቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእርዳታ ደርሷቸው አያውቅም፡፡

በሰብዓዊ እርዳት ስም ለህብረተሰቡ የሚመጣውን ድጋፍ ማግኘት ቀርቶ÷ በቀን ሥራ በሚያገኙት አነስተኛ ገቢ የሸመቱትን እህል እንኳን የሽብር ቡድኑ አባላት በማስፈራራት እና ኃይል በመጠቀም እንደሚቀሟቸው ገልጸዋል፡፡

ድጋፍ ካላደረጋችሁ ልጆቻችሁን ወደ ጦርነት እንወስዳለን እያሉ እንደሚያንገላቷቸውም ተናግረዋል፡፡

ነዋሪው ሲርበው በሰልፍ ወጥቶ እህል ስጡን፤ ርሃቡ ጸናብን ብሎ በመጠየቁ ብዙዎች በጥይት ተገደሉ፤ ከዚያ ወዲህ ደፍረን ለመጠየቅ አልቻልንም ይላሉ፡፡

በጊዜው በተከሰተው ርሃብ ምክንያትም የሰው ሕይወት ማለፉን ነው የገለጹት፡፡

ተከማችቶ የተገኘው የእርዳታ እህል አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መከፋፈሉን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.