Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ክላውድ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ክላውድ” የተሰኘ ተቋማት የተለያዩ መረጃዎችን የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ቤዝ ላይ የሚያገኙበት አሠራር ይፋ አደረገ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት÷ በአገልግሎቱ ተቋማት የዳታ ሴንተር ወይም የመረጃ ማዕከል መገንባት ሳይጠበቅባቸው የፈለጉትን መረጃ ከኢትዮ ቴሌኮም ማግኘት ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርታማነትን የሚያሳድግ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም የመረጃ ማዕከል በመገንባት ለተቋማት ማከራየት መጀመሩን ገልጸው÷ ይህም ተቋማት የመረጃ ማዕከል እስከሚያገኙ ድረስ ኢትዮ ቴሌኮም ያመቻቸው መፍትሔ ነው ብለዋል፡፡

ከቴሌ ክላውድ ጥቅሞች አንዱ “infrastructure as a service“መሆኑን ጠቅሰው÷ በዚህም ተቋማት አፕሊኬሽንና ዳታ ይዞ በመምጣት አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማንኛውንም መረጃ ከኢትዮ ቴሌኮም ማግኘት የሚያስችል “platform as a service“የተሰኘ አገልግሎት ይዞ እንደመጣ አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.