Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ሕዝብ ሕወሓት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የትግራይ ሕዝብ ሕወሓት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊቱን በመንከባከብ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ስለተደበቁ ጀሌዎችና የጦር መሣሪያዎች መረጃ በመስጠት፣ መንገድ በመምራት እና አካባቢውን በመጠበቅ የትግራይ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጋር ተሰልፏል።

ለዚህም መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ቅንጅት ሕወሐትን አስደንግጦታል። በዚህም የተነሣ “ምስለኔዎች ሊያስተዳድሩህ እየመጡ ነው” የሚል ውዥንብር እየነዛ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕወሓት ጋር የታገለው የምስለኔ አስተዳደር እንዲቀር ነው። የምስለኔ አስተዳደርን በክልሎች ላይ እንደገና የዘረጋው ሕወሐት በመሆኑ። የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጆች እንጂ በማንም ሊተዳደር አይገባም። ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ይሄንን አይፈቅድም። ሕወሐትም ይሄንን ያውቃል። ይደብቃል እንጂ።

በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሕወሐትን የምስለኔ ቴአትር፣ በምስለኔነት ለኖረው ለሕወሐት ትቶ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ትብብር እንዲያጠናክር መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.