Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ፎረም በለንደን እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛው የኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ፎረም በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እየተካሔደ ነው፡፡

ፎረሙን÷ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በብሪታንያ የነጋዴዎች ልማት ማኅበር ማዘጋጀታውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በፎረሙ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ባስመዘገቡት አመርቂ ስኬት የተመረጡ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች እና የግል ተቋማት እንዲሁም ከ100 በላይ የዩናይትድ ኪንግደም የቢዝነስ ተቋማት እየተሳተፉ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.