ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር መከሩ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዣኦ ዚዩዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ በክልሉ ለተገኙት አምባሳደር የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፥ የክልሉን አስደናቂ ቅርሶችንም አስጎብኝተዋቸዋል።
አምባሳደሩ የዓለም ቅርስ የሆነውን የሐረር ጁገልን የጎበኙ ሲሆን ፥ በጋራ ጉዳዮች ላይም ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
በቀጣይም ሁለገብ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ያላቸውን ምኞት ገልፀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!