Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ ለሀገራዊ ምክክር ሂደት ገንቢ ሚና ይጫወታል- የፖለቲካ ሣይንስና የሕግ ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለሀገራዊ ምክክር ሂደት ገንቢ ሚና ይጫወታል ሲሉ የፖለቲካ ሣይንስና የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የፖለቲካ ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው በቀለ ሃብታሙ እና በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ዘመድኩን መካሻ እንደገለጹት፥ ተስፋ ሰጭው የሰላም ስምምነት ዜጎችን በሚፈለገው ደረጃ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማገዝ የምክክር ሂደቱን መስመር ያሲዛል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፥ ኮሚሽኑ ብዝሃ ሐሳቦች የሚስተናገዱበት ዐውድ እንዲፈጠር እየሠራ መሆን ጠቁመዋል፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.