Fana: At a Speed of Life!

ጋዜጠኞችና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ዓለም አቀፉን የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ እንዲያስተዋውቁ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋዜጠኞች እና የመንግሥት ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ዓለም አቀፉን የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በማስተዋወቅ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች እና ለመንግሥት ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ዓለም አቀፉን የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማብራሪያው ባለሙያዎቹ ኢትዮጵያ ስለምታስተናግደው ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ለማህበረሰቡ የማሳወቅ ስራ እንዲሠሩ የሚያስችል ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጋዜጠኞች እና የመንግሥት ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ጉባዔውን በማስተዋወቅ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በውይይቱ ስለ ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ምንነት፣ ስለሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም እንዲሁም ጉባዔውን ለማስተዋወቅ መሠራት ስላለባቸው ሥራዎች ተነስቷል።

ጉባኤው ከሕዳር 19 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሔድ እና ከ2ሺህ 500 በላይ እንግዶች ይሳተፉበታል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.