Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሆለታ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት የማስተዋወቅ መርሐ ግብር በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በሆለታ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መርሐ ግብሩን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር በሆለታ የግብርና ምርምር ማዕከል በመገኘት ያስተዋወቁት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ናቸው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና የፌዴራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በማዕከሉም የተለያዩ የእንስሳት ተዋጽኦን ጨምሮ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.