Fana: At a Speed of Life!

“አዲስ የፖለቲካ አዝማሚያዎች እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ሥርዓት ለውጥ” በሚል ርዕስ ለዲፕሎማቶች ሥልጠና ተሠጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “አዲስ የፖለቲካ አዝማሚያዎች እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ሥርዓትለውጥ” በሚል ርዕስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለዲፕሎማቶች ሥልጠና ሠጡ፡፡

ሥልጠናው የተሰጠው በአፍሪካ የአመራር ልኅቀት ማዕከል መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዲፕሎማቶች ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ቆይታም ÷ ስለ ወቅታዊ ዓለምአቀፋዊ አዝማሚያዎች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ ዕድሎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ተቀያያሪ በሆነው የዓለም ሥርዓት እና ተፅዕኖዎቹ በማንሳትም ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ዲፕሎማቶቹ ዓለም አቀፋዊውን አዝማሚያ በጥንቃቄ በመመርመር እንዲራመዱ እና ለመማር ሁልጊዜም ዝግጁ እንዲሆኑ አስገንዝበዋል።

አያይዘውም በናይሮቢ በተካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የትግበራ እንዲሁም በፕሪቶሪያ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ላይ ስለነበራቸው ተሳትፎ ለዲፕሎማቶቹ አስረድተዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት በነበራቸው ቆይታም የቀሰሙትን ትምህርት በተመለከተ አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.