የክልሉ ሕዝብ ሰላሙን በመጠበቅ የልማት ተሳትፎውን ማጠናከር አለበት- አቶ ሙስጠፌ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ በሁሉም የልማት ዘርፍ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አሳሰቡ፡፡
17ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ዛሬ በሶማሌ ክልል ደረጃ በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል።
በአከባበር ሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ባደረጉት ንግግር÷ በዓሉ የፌዴራሊዝም ስርዓት ለሶማሌ ክልል ሕዝብ ያስገኛቸውን ሕገ መንግስታዊ ጥቅሞች የሚዘከርበት ነው ብለዋል።
ሕዝቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ከሌሎች እህት ወንድሞቹ ጋር በመከባበርና በመተባበር በሁሉም የልማት ዘርፍ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበበት አሳስበዋል።
ሕዝቡ ከለውጡ በፊት በነበሩ ዓመታት ምስቅልቅል ሁኔታዎች ቢያጋጥመውም÷ ቋንቋውን በመጠቀምና በመረጣቸው ልጆቹ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳደር ዕድል ተፈጥሯል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መከበሩ በሀገራችንና በክልሉ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችንና የብልፅግና ጉዞ በላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎ ከዳር ለማድረስ መግባባቶች ለመፍጠር እንደሚያግዝም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!