Fana: At a Speed of Life!

ለደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ከፍተኛ ውድመት ለደረሰበት ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል::

ድጋፉ የሙስሊም ኤ አይ ዲ አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር ነው የተደረገው፡፡

በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝነት የተገኘው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ዳንኤል ገብረሚካኤል በተገኙበት ኡስታዝ አቡበክር ድጋፉን አስረክበዋል:፡

የተደረገው ድጋፍ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን እና መድሃኒቶችን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሙስሊም ኤ አይ ዲ አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኝ የሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት መሆኑን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.