የደቡብ ክልል አምስት አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋመ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በክልሉ ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን መታገል የሚያስችል አምስት አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡
በየደረጃው የሚፈፀመውን ሌብነት እና ብልሹ አሠራር በመታገል ረገድ የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ ርስቱ ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ጥቆማ መቀበል የሚያስችሉ የስልክ አድራሻዎች ይፋ ይደረጋሉ ማለታቸውን የደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮሚቴው አባላት ሥራቸውን በላቀ ቁርጠኝነትና በውጤታማነት እንዲያከናውኑ÷ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ አቶ ርስቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡