Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ – አሜሪካ የመሪዎች ጉባዔ በዋሺንግተን እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚሳተፉበት የአፍሪካ – አሜሪካ የመሪዎች ጉባዔ በአሜሪካ ዋሺንግተን እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው አፍሪካ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል ተብሏል፡፡

ዛሬ ቢዝነስ ላይ ትኩረት አድርጎ በሚመክረው ፎረም ላይ ከ300 የሚበልጡ የአሜሪካ እና የአፍሪካ ኩባንያዎች ዋና ሥራ አሥፈፃሚዎች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ አመራሮች እንደሚሳተፉ የአሜሪካ መንግስት ብሔራዊ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፎረሙ መዋዕለ-ንዋይ በማፍሰስ የጤናውን ዘርፍ ፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦት ፣ ግብርና እና ግብርና ተኮር ንግድ እንዲሁም የዲጂታሉን ዘርፍ ለማበረታታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.