በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ744 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ744 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ።
የኦሮሚያ ስራ እድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ በጅማ ከተማ የመቶ ቀናት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የስራ ፈጣሪነት ንቅናቄ ማካሄድ ጀምሯል።
የኦሮሚያ ስራ እድል ፈጠራ እና ክዕሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቲዮስ ሰቦቃ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2015 የበጀት ዓመት በክልሉ 2ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ለአራት ቀናት በሚቆየው መድረክ የስራ ባህልን ማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ የስራ ፈጠራ ስልጠናዎችም መሰጠት መጀመሩንም ነው የተገለጸው።
በወርቅአፈራው ያለው