Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የተጠናው የብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ውይይት ሊደረግበት ነው

አዲስ አበባ፣ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የተጠናው የብዝሃ ቋንቋ መርሐ ትምህርት በተያዘው ሳምንት ውይይት እንደሚደረግበት የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጀው ከሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ጋር የጀመረውን ውይይት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
 
በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በትምህርት ቤቶች የተረጋጋ እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
 
የከተማ አስተዳደሩ እያካሄደ ባለው በዚሁ ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ ÷ የከተማ አስተዳደሩ ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን የብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም አጠናቆ በዚህ ሳምንት ለውይይት እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል፡፡
 
ይህ ካሪኩለም ጸድቆ ወደ ትግበራ የሚገባና በተለይም የከተማዋን ብዝሃነት በብቃት የሚያስተናግድ ስርዓት የሚተገበር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር የቋንቋ ፖሊሲ መሰረት 3 ቋንቋዎችን ራሳቸውን ችለው እንደ አንድ የትምህርት አይነት በትምህርት ቤቶች እንዲሰጡ ለማድረግ እና የባንዲራ እና የመዝሙሩም ጉዳይም መፍትሄ የሚሰጥ እንደሆነ መጠቆማቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.