Fana: At a Speed of Life!

የአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የ10 ኪሎ ሜትር ክብረወሰን ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የ10 ኪሎሜትር ክብረ ወሰን በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ተሰጥቶታል።

አትሌት ያለምዘርፍ በስፔን ካስቴሎን የ10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በማሸነፍ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቧ ይታወሳል።

ክብረ ወሰኑ በኬኒያዊቷ ጆሴሊን ጄፕኮስጊ በ29 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ተይዞ የነበረ ሲሆን ያለምዘርፍ የርቀቱን ክብረወሰን 29 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት ማሻሻሏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.