Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ባለፉት ሁለት ወራት የሰላም መሻሻል የታየበትና የመሰረተ ልማት መልሶ መገንባት ስራ የተከናወነበት መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ወራት የነበረው ሁኔታ የሰላም መሻሻል የታየበትና የመሰረተ ልማት መልሶ መገንባት ስራ የተከናወነበት ነው ሲሉ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን የመንግስት ስራዎች አስተባባሪ ኤልያስ ሽኩር ገለጹ፡፡

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን የፌደራል መንግስት ስራዎች አስተባባሪ ኤልያስ ሽኩር÷ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰሩ ተግባራት ውጤት አስመዝግበዋል ነው ያሉት።

የሽረና አካባቢው ነዋሪዎች በሰላም ስምምነቱ ውጤቶች ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡

በፌደራል መንግስት በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሰላም መረጋጋት እንዲመጣ፣ የጤና ተቋማት መልሰው አገልግሎት እንዲጀምሩ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች እንዲጠናከሩ፣ ማህበራዊ ተቋማት ወደ ስራ እንዲመለሱ ስራዎች መሰራታቸው ተጠቅሷል፡፡

በፌደራል መንግስቱ ህዝቡ አካባቢውንና ሰላሙን እንዲጠብቅ መደረጉም በመድረኩ ተነስቷል።

መከላከያ ሰራዊት በገባባቸው የክልሉ አካባቢዎች ህዝባዊነቱን በተግባር ማሳየቱን የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

12 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ወደ ቤታቸውና መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውም ነው የተገለፀው።

በመንግስት አስተባባሪነት ስራ አቁመው የነበሩ ዘጠኝ ሆስፒታሎችና 13 ጤና ተቋማት ወደ ስራ ተመልሰዋልም ነው የተባለው።

181 መኪኖች እርዳታ ጭነው ወደ ዞኑ መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን÷ትራንስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችም በቅርቡ እንደሚጀምሩም ነው የተገለጸው።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.