Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 8 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት 1 ሺህ 8 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡

በሦስት ዙር ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ 1 ሺህ 8 ዜጎች መካከል 695 ወንዶች ፣ 243 ሴቶች ፣ 70 ሕፃናትና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ዓየር መንገድና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከኅዳር 12 ቀን 2015 ጀምሮ እስከ አሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 21 ሺህ 421 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.