ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 2023 አዲስ ዓመትን ለሚያከብሩ ሀገራት መልካም ምኞታቸውን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት የመልካም ምኞች መልዕክት፥ አዲሱ ዓመት ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘላቂ ሰላም እና ደኅንነት እንዲያመጣ እመኛለሁ ብለዋል።
በጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር ቀመር የሚጠቀሙ ሀገራት 2023 አዲስ ዓመትን ከትናንት ምሽት ጀምረው እየተቀበሉ ነው፡፡