የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 9 የአጭዶ መውቂያ ማሽኖችን ለደንበኞቹ አስረከበ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ዘጠኝ የአጭዶ መውቂያ ማሽኖችን ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ አስረክቧል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው እና በአዲስ አበባ የጀርመን ልማት ባንክ ዳይሬክተር ዲያና ሄድሪክ ተገኝተዋል።
ባንኩ ማሽኖቹን ያስረከበው በቅርንጫፍ እና ዲስትሪክት ለሚገኙ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ማሽኖቹ የምርትን ብክነት ለመቀነስ እና ዘመናዊ እርሻን ለማስፋፋት ሚናቸው የጎላ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ባንኩ ከዚህ ቀደም 52 ማሽኖችን በአራት ዙሮች ለደንበኞቹ ማቅረቡ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡